ትኩስ የስራ ማስታወቂያ በቀጣሪዎች እና በስራ ፈላጊዎች ተወዳጅ የሆነበትን ምስጢር እናካፍላችሁ።
በርካታ ድርጅቶች ከትኩስ የስራ ማስታወቂያ ጋር አብረው በመስራት የሚፈልጉትን ባለሙያ በፍጥነት አግኝተዋል። ሥራቸውንም አቅለዋል። በርካታ ወጣቶችም ከሚፈልጉት ሥራ ጋር ተዛምደዋል። ሥራ ፈላጊዎችን ከቀጣሪዎች ጋር ለማጣመር ትኩስ የስራ ማስታወቂያ ቀላል እና ፈጣን መንገድ ነው።
ለቀጣሪዎች
- የሥራ ማስታወቂያ ለመለጠፍ በጣም ቀላል እና ፈጣን መሆኑ
- እጅግ በጣም ተመጣጣኝ ዋጋ ከብዙ አማራጭ ጋር መኖሩ
- ጎበዝ ሥራ ፈላጊዎችን በፍጥነት ለማገኘት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ ልዩ የአሰራር መንገድ መኖሩ
- በሁሉም የኢትዮጵያ ከፍል ተደራሽ መሆናችን
- በአካባቢ ፣ በጾታ፣ በትምህርት ዝግጀት፣ በልምድ፣ ወዘተ መሰረት ያደረገ ልዩ የማጣመሪያ ስርዓት ያለን መሆኑ ፤ ይህም የቀጣሪዎችንም ሆነ የስራ ፈላጊዎችን ጊዜ ይቆጥባል።
- መመዝገብ፣ CV ማጣራት፣ ለፈተና መለየት፣ መፈተን፣ የክህሎት ስልጠና መስጠት እና የመሳሰሉትን ተጨማሪ ስራዎችን በመስራት የቀጣሪዎችን ጊዜ መቆጠባችን
- ልዩ የማማከር አገልግሎት መስጠታችን
- ለለጠፍናቸው ማስታወቂያዎች የሚፈለገው ባለሙያ ካልተገኘ 100 % ክፍያ ተመላሽ ማድረጋችን።
ለስራ ፈላጊዎች
- ቀላል እና ፈጣን በመሆናችን ሥራ ለመፈለግ የሚወስደውን ጊዜ እና ገንዘብ መቀነሳችን
- ለስራ ፈላጊዎች ሥራ እንዲያገኙ ነፃ ሙያዊ እገዛ መስጠታችን
- ከስራ በተጨማሪ የነጻ ስኮላርሽፕ እና አጫጭር የሙያ ስልጠናዎች ለሥራ ፈላጊዎች ማቅረባችን
- ሥራ ፈላጊዎች የሚያነሷቸውን ማንኛውም ጥያቄዎች ፈጣን መልስ መስጠታችን
- የሥራ ማስታወቆያዎችን አጭር እና ግልጽ በሆነ መልኩ በማህበራዊ ሚዲያ ማውረባችን የበለጠ ጊዜ ቆጣቢ ማድረጋችን።
- በሁሉም ፕላትፎርሞቻችን ከማስታወቂያ ውጭ ሌሎች የማይገናኙ ( ዝባዝንኬ) ጉዳዮችን አለመለጠፋችን
- ሁሉንም አገልግሎት በነጻ ፣ በታማኝነት፣ እና በቅንነት ማቅረባችን
ለሁሉም ምስክሮቻችን በቀጣሪዎች እና በስራ ፈላጊዎች የሚሰጡን አውንታዊ አስተያየቶች ናቸው።